0%

መለያዎችን እና መተግበሪያዎችን ከበይነመረብ አደጋዎች መጠበቅ

May 27, 2025 - ከሳይበር ጥቃት እና ደጋዎች መጠበቅ

ጠንካራ የይለፍ ቃል መፍጠር (Strong Password)

የኢሜይሎች፣ የይለፍ ቃሎች፣ የማህበራዊ ሚዲያ መለያዎች፣ የጽሁፍ መልእክት መላላኪያ መተግበሪያዎች እና የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ጥበቃ የህብረተሰቡ የበይነመረብ ስጋቶች ጥበቃ ወሳኝ አካል ነው።

በተጨማሪም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሂደቶች እና መመሪያዎችን መከተል እና ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

  • ከ12 ፊደሎች ያላነሱ ጠንካራና ውስብስብ የይለፍ ቃላትን በመጠቀም አቢይ ሆሄያት (A-Z) እና ንዑስ ሆሄያት ጥምር ያካትቱ ፊደሎች (a-z)፣ ከቁጥሮች እና ምልክቶች (#,$,%,@,&,!) ያካትቱ
  • ከተቻለ ሙሉ ዓረፍተ ነገሮችን እንደ የይለፍ ቃል ይጠቀሙ(ለምሳሌ TH1515@5TR0NG P@55) እና አንዳንድ ፊደሎች በልዩ ምልክቶች ይተኩ
  • እንደ ግል መረጃ ስልክ ቁጥር፣ የመኖሪያ አድራሻ፣ የትውልድ ቀን፣ ወዘተ ባሉ የይለፍ ቃሎች ውስጥ ከመጠቀም ይቆጠቡ፣
  • የይለፍ ቃሎች በቀላሉ ሊገመቱ የማይቻሉና እና በመዝገበ ቃላት ውስጥ የተካተቱ ባይሆኑ ይመረጣል
  • ተከታታይ እና ቅደም ተከተል ፊደላትን ለምሳሌ (ABCD12345 , QWERTY, ASDZXC) ከመጠቀም ይቆጠቡ
  • ከተቻለ ልዩ እና የታመኑ የይለፍ ቃል አስተዳዳሪ መተግበሪያዎችን ይጠቀሙ
  • የይለፍ ቃሎችን እንደ ሞባይል ስልኮች፣ ኮምፒውተሮች ወይም የጽሁፍ ወረቀቶች ያሉ ደህንነቱ ያልተጠበቁ ቦታዎች ከማስቀመጥ ተቆጠብ
  • የይለፍ ቃላትን ከማጋራት ወይም በሌሎች ሰዎች ፊት በሚታይ መንገድ ከማስገባት ተቆጠብ • ማናቸውንም የይለፍ ቃላትዎን ተጠልፈዋል ብለው ከጠረጠሩ ወዲያውኑ ይለውጡ ።
  • የመለያዎችዎን ይለፍ ቃል በመደበኝነት ይቀይሩ እንዲሁም ከቀድሞዎቹ የተለየ አዲስ የይለፍ ቃል ይፍጠሩ።
  • የይለፍ ቃል መልሶ ማግኛ ጥያቄዎችን በሚመርጡበት ጊዜ በደንብ ይጠንቀቁ። የይለፍ ቃሉን ለማስታወስ የሚጠቀሙት መልሶ ማግኛ ጥያቄ በቀላሉ የሚገመት ኣያድርጉ (ለምሳሌ የአባት ስም እንደ መልሶ ማግኛ ጥያቄ መምረጥ አይመከርም)።
  • ማናቸውም መተግበሪያዎች ላይ የይለፍ ቃሎችን ከማስቀመጥ ተቆጠብ

Play Cover Track Title
Track Authors