0%

የማህበራዊ ሚዲያ መለያዎች ጥበቃ

May 27, 2025 - ከሳይበር ጥቃት እና ደጋዎች መጠበቅ

ከላይ የተጠቀሱትን የይለፍ ቃል መምረጫ መስፈርቶች ያክብሩ።

  • በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አዲስ መለያ ለመክፈት ሲያስቡ አስፈላጊ የሆነውን ትንሹን መረጃ ብቻ ያቅርቡ
  • የመለያ ቁልፎን ደህንነት ለመጨመር የላቁ የደህንነት ቅንብሮችን በመገምገም ይተግብሩ ፥፥ባለ ሁለት ፋክተር ማረጋገጫን ማግበር ፣ የመለያ ዝርዝሮች መዳረሻን መገደብ፣ የግላዊነትን መረጃን መገደብ እንዲሁም የመለያ ቁልፎን ደህንነት በሚጠራጠሩበት ጊዜ ተገቢውን የማስጠንቀቂያ ማንቂያ ዘዴን ይተግብሩ
  • ስለምትለጥፉት ዝርዝር የግል እና ቤተሰብ መረጃ ይጠንቀቁ፥። መረጃ ከታተመ በኋላ መቆጣጠር አስቸጋሪ ስለሆነ
  • ጎጂ እና ህገወጥ በመሳሰሉት የሳይበር እንቅስቃሴዎች ውስጥ መዝረፍ፣ ስም ማጥፋት፣ ሃይማኖትን ወይም እምነትን መስደብ ፣ ሌሎችን ማስፈራራት እና እነሱን መጉዳት ከመሳሰሉት ድርጊቶች እራስዎን ይቆጠቡ
  • ከታመኑ ሰዎች ጋር ብቻ መገናኘትዎን ያረጋግጡ ። የማያውቁት እና እርስዎን እንደ ጓደኛ ሊጨምሩዎት የሚጠይቁ መልዕቶችን በጥንቃቄ የመልከቱ።
  • ካልታወቀ ምንጭ ለሚላኩለት ማንኛውም ንጝሮች ምላሽ ከመስጠት ይቆጠቡ ፣
  • በተለይም አንዳንዶች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሆን ብለው ወይም ባለማወቅ ማንነታቸው ሲቀይሩ ይስተዋላሉ ለምሳሌ (ዕድሜ፣ ስም፣ ጾታ እና ምስል) ።
  • ትክክል ያልሆነ እና ሀሰተኛ መረጃን ከመለጠፍ ወይም እንደገና ከመለጠፍ የቆጠቡ
  • የማህበራዊ ሚዲያ መለያዎች ጥበቃ (Instagram፣ Twitter፣ Facebook) LinkedIn፣ Snapchat…)
  • ከማያውቋቸው ሰዎች የጓደኝነት ጥያቄዎችን ከመቀበል በፊት በገጻቸው ላይ የተለጠፉ ፎቶዎቻቸው እና የጓደኞቻቸው ዝርዝር ያረጋግጡ
  • የማህበራዊ ሚዲያ መለያዎቾን ከሌሎች ጋር ከመለዋወጥ እንዲሁም በማንኛውም ሁኔታ የእርስዎን መለያዎች ለሌሎች ለማጋራት አይፍቀዱ
  • ማህበራዊ ሚዲያን ተጠቅመው ከጨረሱ በኋላ መለያዎችዎ ዘግተው ይውጡ።
  • የማህበራዊ ሚዲያ መለያዎችዎ ከእርስዎ ጋር የተገናኙ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የገል የሞባይል ስልክ ቁጥራቹህ ጋር መገናኘቱን ያረጋግጡ፣ ይህም የማህበራዊ ሚዲያ መለያዎችዎ ከጠፋ መልሶ ለማግኘት ቀላል ያደርገዋል።
  • ማንኛውንም ደህንነታቸው ካልተጠበቁ ምንጮች ያልተጠበቁት አገናኞች ሲያጋጥሞት ጠቅ ከማድረግ ይቆጠቡ

 

Play Cover Track Title
Track Authors