ከላይ የተጠቀሱትን የይለፍ ቃል መምረጫ መስፈርቶች ያክብሩ።
- በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አዲስ መለያ ለመክፈት ሲያስቡ አስፈላጊ የሆነውን ትንሹን መረጃ ብቻ ያቅርቡ
- የመለያ ቁልፎን ደህንነት ለመጨመር የላቁ የደህንነት ቅንብሮችን በመገምገም ይተግብሩ ፥፥ባለ ሁለት ፋክተር ማረጋገጫን ማግበር ፣ የመለያ ዝርዝሮች መዳረሻን መገደብ፣ የግላዊነትን መረጃን መገደብ እንዲሁም የመለያ ቁልፎን ደህንነት በሚጠራጠሩበት ጊዜ ተገቢውን የማስጠንቀቂያ ማንቂያ ዘዴን ይተግብሩ
- ስለምትለጥፉት ዝርዝር የግል እና ቤተሰብ መረጃ ይጠንቀቁ፥። መረጃ ከታተመ በኋላ መቆጣጠር አስቸጋሪ ስለሆነ
- ጎጂ እና ህገወጥ በመሳሰሉት የሳይበር እንቅስቃሴዎች ውስጥ መዝረፍ፣ ስም ማጥፋት፣ ሃይማኖትን ወይም እምነትን መስደብ ፣ ሌሎችን ማስፈራራት እና እነሱን መጉዳት ከመሳሰሉት ድርጊቶች እራስዎን ይቆጠቡ
- ከታመኑ ሰዎች ጋር ብቻ መገናኘትዎን ያረጋግጡ ። የማያውቁት እና እርስዎን እንደ ጓደኛ ሊጨምሩዎት የሚጠይቁ መልዕቶችን በጥንቃቄ የመልከቱ።
- ካልታወቀ ምንጭ ለሚላኩለት ማንኛውም ንጝሮች ምላሽ ከመስጠት ይቆጠቡ ፣
- በተለይም አንዳንዶች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሆን ብለው ወይም ባለማወቅ ማንነታቸው ሲቀይሩ ይስተዋላሉ ለምሳሌ (ዕድሜ፣ ስም፣ ጾታ እና ምስል) ።
- ትክክል ያልሆነ እና ሀሰተኛ መረጃን ከመለጠፍ ወይም እንደገና ከመለጠፍ የቆጠቡ
- የማህበራዊ ሚዲያ መለያዎች ጥበቃ (Instagram፣ Twitter፣ Facebook) LinkedIn፣ Snapchat…)
- ከማያውቋቸው ሰዎች የጓደኝነት ጥያቄዎችን ከመቀበል በፊት በገጻቸው ላይ የተለጠፉ ፎቶዎቻቸው እና የጓደኞቻቸው ዝርዝር ያረጋግጡ
- የማህበራዊ ሚዲያ መለያዎቾን ከሌሎች ጋር ከመለዋወጥ እንዲሁም በማንኛውም ሁኔታ የእርስዎን መለያዎች ለሌሎች ለማጋራት አይፍቀዱ
- ማህበራዊ ሚዲያን ተጠቅመው ከጨረሱ በኋላ መለያዎችዎ ዘግተው ይውጡ።
- የማህበራዊ ሚዲያ መለያዎችዎ ከእርስዎ ጋር የተገናኙ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የገል የሞባይል ስልክ ቁጥራቹህ ጋር መገናኘቱን ያረጋግጡ፣ ይህም የማህበራዊ ሚዲያ መለያዎችዎ ከጠፋ መልሶ ለማግኘት ቀላል ያደርገዋል።
- ማንኛውንም ደህንነታቸው ካልተጠበቁ ምንጮች ያልተጠበቁት አገናኞች ሲያጋጥሞት ጠቅ ከማድረግ ይቆጠቡ

Previous
ጠንካራ የይለፍ ቃል መፍጠር (Strong Password) የኢሜይሎች፣ የይለፍ ቃሎች፣ የማህበራዊ ሚዲያ መለያዎች፣ የጽሁፍ መልእክት መላላኪያ መተግበሪያዎች እና የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ጥበቃ የህብረተሰቡ የበይነመረብ ስጋቶች ጥበቃ ወሳኝ አካል ነው። በተጨማሪም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሂደቶች እና መመሪያዎችን መከተል እና ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ከ12 ፊደሎች ያላነሱ ጠንካራና ውስብስብ የይለፍ ቃላትን በመጠቀም [...]