ማልዌር የራስ ወዳልሆነ ኮምፒውተር ህገወጥ በሆነ መንገድ ለመግባት ወይም ጉዳት ለማድረስ ታስቦ የሚዘጋጅ አጥፊ ሶፍትዌር ነው፡፡ ማልዌር /Malware/ የሚለው ቃል “malicious software” ከሚሉ ሁለት የእንግሊዘኛ ቃላት በመውሰድ የተሰጠ ስያሜ ነው:: አጥፊ ሶፍትዌሮች ዓይነታቸው የሚለያይ ሲሆን ስፓይዌር (spyware)፣ ራንሰምዌር (ransomware)፣ ዋርም /worms/፣ ትሮጃን ሆርስ /Trojan horses/፣ አድዌር /adware/ ወይም ማንኛውም ዓይነት ኮምፒውተርን ሊጎዳ የሚችል ኮድ የያዘ ሊሆን ይችላል፡፡
ኮምፒውተር በተለያዩ ምክንያቶች ለማልዌር ጥቃት ሊጋለጥ የሚችል ሲሆን ከነዚህም መካከል በኦፕሬቲንግ ሲስተም ዲዛይን ላይ በሚፈጠር ችግር፣ በአንድ ኔትወርክ ውስጥ ሁሉም ኮምፒውተሮች ተመሳሳይ ኦፕሬቲንግ ሲስተም የሚጠቀሙ ከሆነ ወይም ለተጠቃሚዎች በርካታ ፈቃዶችን የሚሰጥ ከሆነ በቀላሉ ለጥቃት ሊጋለጥ ይችላል፡፡
ማልዌር ጥቃትን ለመከላከል ሊወሰዱ ከሚገቡ ጥንቃቄዎች መካከል በኢ-ሜይል የሚላኩ አባሪዎችን ከመክፈታችን በፊት ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ፤ ከአጠራጣሪ ድረ-ገጾች መራቅ፤ ዝመናዎችን በየጊዜው እየተካታተሉ መጫን እና ጥራት ያላቸው ፀረ-ቫይረስ ፕሮግራሞችን መጠቀም ይመከራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ወሳኝ መረጃዎችን እንደመጠባበቂያ በማስቀመጥ ጥቃት ቢደርስብን እንኳን የጉዳቱን መጠን በእጅጉ መቀነስ ይቻላል፡
ራንሰምዌር (Ransomware) ወሳኝ መረጃን ወይም መላውን መሳሪያ የሚመሰጥር ሲሆን (ኮምፒውተር ወይም ስማርት ስልክ) ተጠቃሚው መረጃውን(ውሂብ) እንዳይደርስበት ያደርጋል። ከዚያም ጠላፊው ተጎጂውን የተወሰነ ገንዘብ እንዲከፍል በቢት ኮይን ፡ መልክ ይጠይቃል
ይህም ጠላፊውን ለመፈለግ አስቸጋሪ ስለሚያደርገው ነው። ይህን ከተደረገ ጠላፊው የሚስጥር ቁልፉን ለመላክ በምላሹ ውሂቡ እና መላውን መሳሪያ እንደገና መደበኛ ወደ ሆነ ይዞታ ለመመለስ ቃል ይገባል (ይህ ዋስትና አይሰጥም ፣ ስለዚህ ቤዛውን ለመክፈል ፈጽሞ አይመከርም)።
ራንሰምዌር (Ransomware) ጥንቃቄ
Play | Cover | Release Label |
Track Title Track Authors |
---|